ልዩ የክረምት ትምህርት
ለተማሪዎች ልዩ የሶስት ወር የሚቆይ የክረምት የቁርዓን ትምህርት የተዘጋጀ ሲሆን በፕሮግራሙ ውስጥም ቁርዓን ለጀማሪዎች እንዲሁም የቁርዓን ተጅዊድ እና የቁርዓን ሂፍዝ መርሃ ግብር ተካቶል፡፡
ልዩ የክረምት የቁርዓን ትምህርት ከመደበኛው የቁርዓን ተንዚል ኦንላይን የቁርዓን ትምህርት ልዩ የሚደርገው ተማሪዎች በክረምት ወቅት ጊዜቸው በስፋት ቁርዓን ላይ እንዲሳልፉ ለማድረግ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰፊ ጊዜ በመስጠት ለውጥ እንዲመጡ ታስቦ የተዘጋጀ ፕሮግራም ነው፡፡ በዚህ የሶስት ወር መርሃ ግብርም የሚከተሉትን ትምህርቶች ተካቶል፡፡
- ቁርዓን ለጅማሪዎች ቁርዓን ተጅዊድ ቁርዓን ሂፍዝ
- የተለያዩ የቁርዓን ቃላቶች ትርጉም ፍች እንዲሁም የተለያዩ አጋጅ የሞባይልና አፕልኬሽኖች ና የተለያዩ አጋጅ የትምህርት መሳሪዎች የተዘጋጁ መሆናቸው
- ለሴት ተማሪዎች በሴት ኡስታዞች ፕሮግራሙ የሚሰጥ ይሆናል
በዚህ የክረምት ፕሮግራም ላይ እናቶች እንዲሳተፉ የሚበረታታ ሲሆን ከልጆቻቸው ጋር በመሆን የፕሮግራሙ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይበረታታሉ፡፡